የፓስፖርትና ሊሴ ፓሴ አገልግሎት

 

በኢፌዲሪ ኤምባሲ ካንቤራ የሚሰጡ የቆንስላ አገልግሎቶች

አገልግሎቶችን ለማግኘት የሚያስፈልጉ ቅድመ-ሁኔታዎች

ፓስፖርትና ሊሴፓሴ

ማኑዋል ፓስፖርት

 • እባክዎ አገልግሎቱን አዘጋጅተን እንድንስጥዎ በጥንቃቄ አንብበው አስፈለጊውን ማስረጃዎች ከነ ፎቶ ኮፒው አያይዘው ያቅርቡ/ይላኩ፡:
 • አዲሱ ማሽን ሪደብል ፓስፖርት ለማግኘት የጣት አሻራ ማቅረብ ያስፈልጋል፡፡ ነገር ግን ከዚህ ቀደሞ አዲሱን ፓስፖርት ሲወስዱ የጣት አሻራ ሰጥተው ከነበረ በድጋሚ መስጠት አያስፈልግም፡፡ እንዲሁም ከ14 አመት በታች የሆኑ ህጻናት አሻራ መስጠት አይጠበቅባቸውም፡፡ የጣት አሻራ ለመስጠት ወደ ኤምባሲው መምጣት ወይም በአቅራቢያዎት የሚገኝ የጣት አሻራ የማንሳት ስልጣን ያለው አካል ጋር መሄድ ይችላሉ፡፡
 • ኤምባሲው ፓስፖርትዎን ለማዘጋጀት ተጨማሪ ማስረጃዎች እንዲያቀርቡ ሲጠይቅ እባክዎ ማስረጃውን በአሰቸኳይ ይላኩልን፡፡
 • የፓስፖርት እድሳት የአገልግሎቱ ጊዜ ከማለቁ ከ6 ወር በፊት መቅረብ አለበት።
 • በፖስታ ቤት አማካኝነት ፓስፖርት የምትጠይቁ ባለጉዳዮች መላኪያም ሆነ መመለሻ ፖስታ መጠቀም የሚኖርባችሁ Tracking Number ባለው መሆን ይገባዋል፡፡
 • የላኩት ፖስታ ወደ ኤምባሲያችን ለመድረሱ ፖስታውን በላኩበት የTracking Number በመጠቀም ለማወቅ ይችላሉ፡፡
 • የፓስፖርትዎ ማመልከቻ ኤምባሲው ከተረከበት ከአንድ ወር በኋላ ያለበትን ደረጃ ለማወቅ በላኩት የመመለሻ ፓስታ Tracking Number በመጠቀም ያጣሩ፡፡

አዲስ ፓስፖርት ለማግኘት

 • የሌላ አገር ዜግነት አለማግኘታቸውን የሚገልጽ የጽሁፍ ማመልከቻ ማቅረብ፣
 • ኢትዮጵያዊ መሆኑን የሚያረጋግጥ በቂ ማስረጃ፣( የልደት ማሰረጃ፣ ከወረዳ የተሰጠ የነዋርነት ማሰረጃ ወዘተ)
 • የተሞላ የፓስፖርት መጠየቂያ ፎርም ፣ (እባክዎን ፎርሙን ለማውረድ እዚህ ጋር ይጫኑ)
 • የጣት አሻራ መስጠት፣ (ቀደም ሲል ፓስፖርት ሲያወጡ የጣት አሻራ ከሰጡ በድጋሚ መስጠት አያስፈልግም)
 • አራት መጠኑ 3X4cm የሆነ ፎቶግራፍ፣
 • የአገልግሎት ክፍያ መፈጸም፣

በጠፋ ወይም በተበላሸ ፓስፖርት ምትክ ለማግኘት

 • የፓስፖርትና ቪዛ ፎቶ ኮፒ፣
 • የጽሁፍ ማመልከቻ ማቅረብ፣
 • የተሞላ የፓስፖርት መጠየቂያ ፎርም፣ (እባክዎን ፎርሙን ለማውረድ እዚህ ጋር ይጫኑ)
 • የጣት አሻራ መስጠት፣ (ቀደም ሲል ፓስፖርት ሲያወጡ የጣት አሻራ ከሰጡ በድጋሚ መስጠት አያስፈልግም)
 • ፓስፖርቱ የጠፋ ከሆነ ይህንኑ የሚያረጋግጥ የፖሊስ ማስረጃ፣
 • አራት መጠኑ 3x4cm የሆነ ፎቶግራፍ፣
 • የአገልግሎት ክፍያ መፈጸም፣
 • [/list]

  የቀድሞ ፓስፖርት ለማደስ

  • የሌላ አገር ዜግነት አለማግኘታቸውን የሚገልጽ የጽሁፍ ማመልከቻ ማቅረብ፣
  • የተሞላ የፓስፖርት ዕድሳት መጠየቂያ ፎርም፣ (እባክዎን ፎርሙን ለማውረድ እዚህ ጋር ይጫኑ)
  • የሚታደሰው ፓስፖርት ፎቶኮፒ፣
  • አራት መጠኑ 3x4cm የሆነ ፎቶግራፍ ማቅረብ፣
  • የጣት አሻራ፣ (ቀደም ሲል ፓስፖርት ሲያወጡ የጣት አሻራ ከሰጡ በድጋሚ መስጠት አያስፈልግም)
  • የአገልግሎት ክፍያ መፈጸም፣

  የአገልግሎቱ ክፍያ መጠን

  pp fee2

  ሊሴ ፓሴ ለማግኘት

  • ኢትዮጵያዊ መሆኑን የሚያረጋግጥ በቂ ማስረጃና የጽሁፍ ማመልከቻ፣
  • የተሞላ የሊሴ ፓሴ መጠየቂያ ፎርም፣ (እባክ ዎን ፎርሙን ለማውረድ እዚህ ጋር ይጫኑ)
  • አራት መጠኑ 3x4cm የሆነ ፎቶግራፍ ማቅረብ፣
  • የጣት አሻራ፣
  • 65 AUD የአገልግሎት ክፍያ መፈጸም፣
  Pin It

  Leave a Reply

  Your email address will not be published.