የትውልድ ኢትዮጵያ መታወቂያ አገልግሎት

ጳጉሜ 2 ቀን 2007 ዓ.ም

አዲስ ማስታወቂያ

የአገልግሎት ጊዜው ያበቃ የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ ለያዛችሁ ትውልድ ኢትዮጵያዊያን በመሉ

ከታህሳስ 1 ቀን 2007 ዓ.ም( እኤአ ድሰምቤር 10, 2014) ጀምሮ የአገልግሎት ጊዜው ያበቃ የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ የያዙ የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆኑ የውጭ አገር ዜጎች መታወቂያቸው እንዲታደስላቸው አገልግሎት በሚጠይቁበት ወቅት የቅጣት ክፍያ እንዲከፍሉ ተወስኗል።

ሆኖም ግን የቅጣት ክፍያው ተግባራዊ ከመደረጉ በፊት የመሸጋገሪያ ጊዜ መስጠት የታመነበት በመሆኑ እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2007 ዓ.ም( እኤአ ኦገስት 6, 2015) ድረስ ከቅጣት ነፃ የተወላጅነት መታወቂያውን ያለ ቅጣት እንዲያሳድሱ በተወሰነው መሠረት አንዳንድ ትውልድ ኢትዮጵያዊያን እድሉን በመጠቀም በወቅቱ የእድሳት ጥያቄ ያቀረቡ ቢሆንም በርካታ ትውልድ ኢትዮጵያዊያን የእድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል የተቀመጠው የጊዜ ገደብ በድጋሚ ላልተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም ተወስኗል

በመሆኑም በአውስትራሊያና ኒውዝላንድ ነዋሪ የሆናችሁ እና የአገልግሎት ጊዜው ያበቃ የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ የያዛችሁ ትውልድ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ የመታወቂያ እድሳት አገልግሎት ጥያቄያችሁን በተቻለ ፍጥነት ለኤምባሲያችን እንድታቀርቡ በአክብሮት ለማሳወቅ እንወዳለን።

የኢፌዲሪ ኤምባሲ

ካንቤራ

ሰኔ 22 ቀን 2007 ዓ.ም

ማስታወቂያ

የአገልግሎት ጊዜው ያበቃ የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ ለያዛችሁ ትውልድ ኢትዮጵያዊያን በመሉ

ከታህሳስ 1 ቀን 2007 ዓ.ም( እኤአ ድሰምቤር 10, 2014) ጀምሮ የአገልግሎት ጊዜው ያበቃ የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ የያዙ የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆኑ የውጭ አገር ዜጎች መታወቂያቸው እንዲታደስላቸው አገልግሎት በሚጠይቁበት ወቅት የቅጣት ክፍያ እንዲከፍሉ መደረጉ ይታወሳል።

ሆኖም ግን የቅጣት ክፍያው ተግባራዊ ከመደረጉ በፊት የመሸጋገሪያ ጊዜ መስጠት የታመነበት በመሆኑ የአገልግሎት ጊዜው ያበቃ የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ የያዙ ትውልድ ኢትዮጵያዊያን እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2007 ዓ.ም( እኤአ ኦገስት 6, 2015) ድረስ ከቅጣት ነፃ የተወላጅነት መታወቂያ ካርዳቸውን እንዲያሳድሱ እና ከነሐሴ 1 ቀን 2007 ዓ.ም( እኤአ ኦገስት 7, 2015) ጀምሮ ቅጣቱ ተግባራዊ እንዲሆን ተወስኗል።

በመሆኑም በአውስትራሊያና ኒውዝላንድ ነዋሪ የሆናችሁ እና የአገልግሎት ጊዜው ያበቃ የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ የያዛችሁ ትውልድ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2007 ዓ.ም(እኤአ ኦገስት 6, 2015) ድረስ የመታወቂያ እድሳት አገልግሎት ጥያቄያችሁን ለኤምባሲያችን እንድታቀርቡ እየገለጽን፣ ከነሐሴ 1 ቀን 2007 ዓ.ም( እኤአ ኦገስት 7, 2015) ጀምሮ ቅጣቱ ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑን በአክብሮት ለማሳሰብ እንወዳለን።

የኢፌዲሪ ኤምባሲ

ካንቤራ

 

አገልግሎቶችን ለማግኘት የሚያስፈልጉ ቅድመ-ሁኔታዎች

አዲስ የትውልድ ኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ለማግኘት

 •  ዜግነት ካገኘበት አገር የተሰጠ አገልግሎቱ የፀና ፓስፖርት  ሁለት ኮፒ፣
 • በትውልድ ኢትዮጵያዊ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ (የአመልካቹ  የቀድሞ የኢትዮጵያ ፓስፖርት ከነኮፒው፣ ወይም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተረጋገጠ የአመልካቹ የልደት ሰርቲፊኬት ሁለት ኮፒ፣ ወይም  ከአትዮጵያ ፍርድ ቤት የተሰጠና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተረጋገጠ የወላጆች ወራሽነት ማሰረጃ  ሁለት ኮፒ፣ ወይም  ከኢትዮጵያ ፍርድ ቤት የተሰጠና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተረጋገጠ በኢትዮጵያን ወላጆቹ ለጉዲፈቻ የተሰጠ መሆኑን የሚያሳይ ማሰረጃ  ሁለት ኮፒ፣ ወይም  ከኢትዮጵያ ፍርድ ቤት የተሰጠና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተረጋገጠ የኢትዮጵያን ተወላጅነት የሰው ወይም የሰነድ ምስክርነት  ማሰረጃ  ሁለት ኮፒ፣ወይም  ከኢትዮጵያ ፍርድ ቤት የተሰጠና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተረጋገጠ የኢትዮጵያ ተወላጅነቱን በተጨባጭ የሚያረጋግጥ አባቱ ወይም እናቱ ወይም  አያቱ ወይም ቅድመ አያቱ ቢያንስ በአንዱ የኢትዮጵያ ዜግነት ይዞ የነበረ መሆኑን የሚረጋግጥ ማሰረጃ  ሁለት ኮፒ፣  .)
 • የአመልካቹ የጣት አሻራ ከነኮፒው ፣
 • የተሞላ የአገልግሎት መጠየቂያ ፎርም (ቅጽ 1 ) ሁለት ኮፒ ፣ (እባክዎን ፎርሙን ለማውረድ እዚህ ጋር ይጫኑ)
 • ሶስት መጠኑ 3X4cm የሆነ ፎቶግራፍ፣
 • የአገልግሎት ክፍያ መፈጸም፣

አካለ መጠን ላልደረሰ (ከ18 ኣመት በታች) የኢትዮጵያ ተወላጅ ህፃን የትውልድ ኢትዮጵያ መታወቂያ ለመጠየቅ

 • አገልግሎቱ የፀና የወላጅ ፓስፖርት ሁለት ኮፒው፣
 • አገልግሎቱ የፀና የወላጅ የትውልድ ኢትዮጵያ መታወቂያ ካርድ ሁለት ኮፒው፣
 •  የልጁ የተረጋገጠ የልደት ሰርቲፊኬት ሁለት ኮፒ
 • የተሞላ የአገልግሎት መጠየቂያ ፎርም (ቅጽ 1 )፣ (እባክዎን ፎርሙን ለማውረድ እዚህ ጋር ይጫኑ)
 •  የህጻኑ ሶስት መጠኑ 3X4cm የሆነ ፎቶግራፍ፣
 • የህጻኑ ዕድሜ 14ና ከዚያ በላይ ከሆነ የልጁ የጣት አሻራ ከነኮፒው ፣
 • የአገልግሎት ክፍያ መፈጸም፣
 • [/list]

  የውጭ አገር ዜጋ ለሆኑ ባል ወይም ሚስት  የትውልድ ኢትዮጵያ መታወቂያ ለማግኘት

  • አገልግሎቱ የፀና የአመልካቹ ፓስፖርት ሁለት ኮፒ፣
  •  ቢያንስ 2 አመት የሆነው  የተረጋገጠ የጋብቻ ሰርቲፊኬት ሁለት ኮፒ
  • የባል ወይም የሚስት አገልግሎቱ የፀና  የትውልድ ኢትዮጵያ መታወቂያ ሁለት ኮፒ፣
  • የተሞላ የአገልግሎት መጠየቂያ ፎርም (ቅጽ 2 )፣ (እባክዎን ፎርሙን ለማውረድ እዚህ ጋር ይጫኑ)
  •  የአመልካቹ ሶስት መጠኑ 3X4cm የሆነ ፎቶግራፍ፣
  • የአመልካቹ የጣት አሻራ ከነኮፒው ፣
  •  ትዳሩ የፀና ለመሆኑ ሁለቱ ጥንዶች በጋራ የፈረሙት የቃለ መሃላ ማሰረጃ ሁለት ኮፒ ፣ (እባክዎን የቃለ መሃላ ፎርሙን ለማግኘት እዚህ ጋር ይጫኑ)
  • የአገልግሎት ክፍያ መፈጸም፣

  የትውልድ ኢትዮጵያ መታወቂያ ለማደስ

 • አገልግሎቱ የፀና የአመልካቹ ፓስፖርት ሁለት ኮፒ፣
 • አገልግሎቱ ያበቀው መታቂያ ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
 • በትውልድ ኢትዮጵያዊ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ (የአመልካቹ  የቀድሞ የኢትዮጵያ ፓስፖርት ከነኮፒው፣ ወይም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተረጋገጠ የአመልካቹ የልደት ሰርቲፊኬት ሁለት ኮፒ፣ ወይም  ከአትዮጵያ ፍርድ ቤት የተሰጠና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተረጋገጠ የወላጆች ወራሽነት ማሰረጃ  ሁለት ኮፒ፣ ወይም  ከኢትዮጵያ ፍርድ ቤት የተሰጠና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተረጋገጠ በኢትዮጵያን ወላጆቹ ለጉዲፈቻ የተሰጠ መሆኑን የሚያሳይ ማሰረጃ  ሁለት ኮፒ፣ ወይም  ከኢትዮጵያ ፍርድ ቤት የተሰጠና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተረጋገጠ የኢትዮጵያን ተወላጅነት የሰው ወይም የሰነድ ምስክርነት  ማሰረጃ  ሁለት ኮፒ፣ወይም  ከኢትዮጵያ ፍርድ ቤት የተሰጠና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተረጋገጠ የኢትዮጵያ ተወላጅነቱን በተጨባጭ የሚያረጋግጥ አባቱ ወይም እናቱ ወይም  አያቱ ወይም ቅድመ አያቱ ቢያንስ በአንዱ የኢትዮጵያ ዜግነት ይዞ የነበረ መሆኑን የሚረጋግጥ ማሰረጃ  ሁለት ኮፒ፣  .)
 • የተሞላ የአገልግሎት መጠየቂያ ፎርም ፣ (እባክዎን ፎርሙን ለማውረድ እዚህ ጋር ይጫኑ)
 •  ሶስት መጠኑ 3X4cm የሆነ ፎቶግራፍ፣
 •  መታወቂያው በጋብቻ የተገኘ ከሆነ ትዳሩ የፀና ለመሆኑ ሁለቱ ጥንዶች በጋራ የፈረሙት የቃለ መሃላ ማሰረጃ ሁለት ኮፒ ፣ (እባክዎን የቃለ መሃላ ፎርሙን ለማግኘት እዚህ ጋር ይጫኑ)
 • የአመልካቹ የጣት አሻራ ከነኮፒው (ቀደም ሲል መታወቂያው በወጣበት ጊዜ አሻራ ያልሰጠ ከሆነ ብቻ)፣
 • የአገልግሎት ክፍያ መፈጸም፣
 • [/list]

  የጠፋ ወይም የተበላሸ የትውልድ ኢትዮጵያ መታወቂያ ለመተካት

  • የጽሁፍ ማመልከቻ፣
  • መታወቂያው የጠፋ ከሆነ ይህንኑ የሚያረጋግጥ የፖሊስ ማሰረጃ
  • አገልግሎቱ የፀና ፓስፖርት ኮፒ፣
  •  የጠፋው ውይም የተበላሸ መታወቂያው በጋብቻ የተገኘ ከሆነ ትዳሩ የፀና ለመሆኑ ሁለቱ ጥንዶች በጋራ የፈረሙት የቃለ መሃላ ማሰረጃ ሁለት ኮፒ ፣ (እባክዎን የቃለ መሃላ ፎርሙን ለማግኘት እዚህ ጋር ይጫኑ)
  • የተሞላ የአገልግሎት መጠየቂያ ፎርም ፣ (እባክዎን ፎርሙን ለማውረድ እዚህ ጋር ይጫኑ)
  • የአመልካቹ የጣት አሻራ ከነኮፒው (ቀደም ሲል መታወቂያው በወጣበት ጊዜ አሻራ ያልሰጠ ከሆነ ብቻ)፣
  • አራት መጠኑ 3X4cm የሆነ ፎቶግራፍ፣
  • የአገልግሎት ክፍያ መፈጸም፣

  የአገልግሎቱ ክፍያ መጠን

  ተራ

  ቁ.

  የአገልግሎቱ ዓይነት

  የክፍያ መጠን በAUD

  1

  አዲስ የትውልድ ኢትዮጵያ መታወቂያ ለማውጣት (ለአዋቂዎች)

  አዲስ የትውልድ ኢትዮጵያ መታወቂያ ለማውጣት(18 አመት በታች ለሆኑ ልጆች)

  260

  26

  2

  አገልግሎቱ ያበቃ የትውልድ ኢትዮጵያ መታወቂያ  ለማደስ

  የተበላሸ የትውልድ ኢትዮጵያ መታወቂያ  ለመተካት

  260

  286

  3

  በጠፋ የትውልድ ኢትዮጵያ መታወቂያ ለመተካት(ለመጀመሪያ ጊዜ) 312AUD

  በጠፋ የትውልድ ኢትዮጵያ መታወቂያ ለመተካት(ለሁለተኛ ጊዜ)390AUD

  በጠፋ የትውልድ ኢትዮጵያ መታወቂያ ለመተካት(ለሶስተኛ ጊዜ)520AUD

  የትውልድ ኢትዮጵያ መታወቂያ በወቅቱ  ያላሳደሰ  በየቀኑ የሚከፍለው መቀጮ

  ከ1 እስከ 15 ቀን ካሳለፈ በየቀኑ  3.9 AUD

  ከ15 እስከ 30 ቀን ካሳለፈ በየቀኑ  6.5 AUD

  Pin It

  Leave a Reply

  Your email address will not be published.