ማስታወቂያ

 

ማስታወቂያ
ከኢትዮጵያ ባንኮችና የኢሹራንስ ካምፓኒዎች  አክሲዮን የገዛችሁትውልደ ኢትዮጵያውያን በሙሉ
የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆኑ የውጭ ዜጎችን በትውልድ አገራቸው የተለያዩ መብቶች ተጠቃሚ ለማድረግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 270/94 በሚገባ ባለማስገንዘብ አንዳንድ ትውልደ ኢትዮጵያውያን በፋይናንስ ዘርፍ አክሲዮን ገዝተው በመገኘታቸው የገዙት ገንዘብ በባንኮች መታገዱን በመግለጽ ችግሩ የተፈጠረው ከመረጃና ግንዛቤ ማነስ በመሆኑ ይቅርታ እንዲደረግላቸው በተደጋጋሚ ከዳያስፖራ አባላት ጥያቄ የቀረበ ሲሆን ፣ ይህንኑ ጥያቄ በፍትህ ሚ/ር በኩል አስተያየት እንዲሰጥበት በማድረግ መንግስት ውሳኔ እንዲሰጥበት አድርጓል፡፡
በዚሁ መሰረት አክሲዮን የገዙ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን አክሲዮን የገዙበት ገንዘብ  እ.ኤ.አ እስከ June 30, 2016 ድረስ ከነወለዱ ተሰልቶ ተመላሽ እንዲደረግላቸው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ያሳወቀን በመሆኑ ይህንኑ አውቃችሁ በባንኮችና ኢንሹራንስ ካምፓኒዎች አክሲዮን የገዛችሁ በተላለፈው ውሳኔ መሰረት አክሲዮኑን የገዛችሁበትን መረጃ በመያዝ ገንዘባችሁን ወጪ ማድረግ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

ለበለጠ መረጃ ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ

http://www.ethiopianembassy.org/PDF/Diaspora2016.pdf

Comments are closed.